Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ አዳማ ከተማ ወልቂጤ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ አንድ ጨዋታ ተደርጓል።

እንግዳው ወልቂጤ ከተማ ከአዳማ ከተማ ጋር ተጨውተው አዳማ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ፕሪሚየር ሊጉ ነገም ሲቀጥል ፋሲል ከነማ ከሜዳው ውጭ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ይጫወታል።

እንዲሁም መቐለ 70 እንደርታ በሜዳው ባህር ዳር ከተማን ያስተናግዳል።

ሰበታ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ወላይታ ዲቻ ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ ሃዋሳ ከተማ ከሃዲያ ሆሳዕና፣ ጅማ አባጅፋር ከኢትዮጵያ ቡና እና ስሑል ሽረ ከሲዳማ ቡና ሌሎች የነገ መርሃ ግብሮች ናቸው።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.