Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና፣ ፋሲል ከነማ እና ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የ6ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ተደርገዋል።

አዲስ አበባ ላይ ሃዲያ ሆሳዕናን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና በሰፊ የጎል ልዩነት አሸንፏል።

ቡናማዎቹ ጨዋታውን 5 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

በሌሎች ጨዋታዎች ደግሞ አዳማ ከተማ ከጅማ አባ ጅፋር እንዲሁም ወልቂጤ ከተማ ከስሑል ሽረ ያደረጉት ጨዋታ ያለምን ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

በተመሳሳይ መቐለ ላይ በተደረገ ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከሃዋሳ ከተማ ጨዋታቸውን በአቻ ውጤት አጠናቀዋል።

በሜዳው ድሬዳዋ ከተማን ያስተናገደው ሲዳማ ቡና ደግሞ 2 ለ 1 ተሸንፏል።

ጎንደር ላይ በተደረገ ጨዋታ ባህር ዳር ከተማን ያስተናገደው ፋሲል ከነማ 3 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል።

ሊጉ ነገም ሲቀጥል አዲስ አበባ ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመቐለ 70 እንደርታ ይገናኛሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.