Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት በክልል ከተማዎች በዛሬው ዕለት 5 ጨዋታዎች ተካሂደዋል።

በሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።

በዚህም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሜዳው ውጭ አንድ ነጥብ በማግኘት በ27 ነጥብ የአንደኝነት ደረጃውን ሲያስጠብቅ በተመሳሳይ ፋሲል ከነማም በ26 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ማስጠበቅ ችሏል።

ጅማ ላይ በተካሄደው ሌላኛው ጨዋታ ጅማ አባ ጅፋር ወራጅ ቀጣና የሚገኘውን ድሬዳዋ ከተማን አስተናግዶ 2 ለ 1 አሸንፏል።

ይህንን ተከትሎ ጅማ አባ ጅፋር በጊዜያዊነት አንድ ደረጃን ሲያሻስል በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ በወራጅ ቀጠና መቆየት ግድ ብሎታል።

አዳማ ከተማም ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲን አስተናግዶ 2 ለ 0 በማሸነፍ ደረጃውን ማሻሻል ችሏል።

እንዲሁም ወደ ወላይታ ሶዶ ያቀናው ባህር ዳር ከተማ በወላይታ ድቻ 1 ለ 0 የተሸነፈ ሲሆን ውጤቱን ተከትሎ ወላይታ ድቻ ወደ 4ኛ ደረጃ ከፍ ብሏል።

በሌላኛው ጨዋታ ስሑል ሽረ ከሀዲያ ሆሳዕና 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የፋሲል ከነማው ሙጂብ ቃሲም ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ አንድ ግብ ማስቆጠሩን ተከትሎ የኮኮብ ግቢ አግቢነቱን በ14 ጎሎች መምራት ቀጥሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.