Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማና ሰበታ ከተማ ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 25 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለት ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት ተካሂደዋል።

ጎንደር ላይ ፋሲል ከነማን ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያገናኘው ጨዋታ በፋሲል ከነማ 1 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

የፋሲል ከነማን የማሸነፊያ ጎል የፕሪሚየር ሊጉን ኮኮብ አግቢነት እየመራ የሚገኘው ሙጅብ ቃሲም በ24ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።

ሰበታ ከተማ ከሀድያ ሆሳዕና ያደረጉት ሌላኛው ጨዋታ ደግሞ በሰበታ ከተማ 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

የሰበታን የማሸነፊያ ግቦች ባኑ ዲያዋራ በ7ኛው ደቂቃ እና ፍፁም ገብረማርያም በ81ኛው ደቂቃ ላይ ሲያስቆጥሩ የሀድያ ሆሳዕናን ብቸኛ ግብ ቢስማርክ አፒያ 32ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.