Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ እና ሰበታ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ግንቦት 10፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፐሪሚየርሊግ ፋሲል ከነማ መከላከያን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

ሽመክት ጉግሳ እና ናትናኤል ገብረ ጊዮርጊስ የፋሲል ከነማን የድል ጎሎች ሲያስቆጥሩ አሚን ነስሩ ብቸኛዋን የመከላከያ ጎል አስቆጥሯል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም ፋሲል ከነማ ደረጃውን ሲያስጠብቅ መከላከያ በነበረበት 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ረፋድ 4 ሰዓት በተከናወነ ጨዋታ ወራጅ ቀጠና የሚገኘው ሰበታ ከተማ ወልቂጤ ከተማን በተመሳሳይ 2 ለ 1 አሸንፏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.