Fana: At a Speed of Life!

በፕሪምየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ስሑል ሽረ፣ አዳማ ከተማ እና ወላይታ ድቻ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 12ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት በተለያዩ ከተሞች ተካሂደዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሲዳማ ቡና በአዲስ አበባ ስታዲየም ባካሄዱት ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ 6 ለ 2 በሆነ ሰፊ ልዩነት አሸንፏል።

ኢትዮጵያ ቡናን በአበበ ቢቄላ ስታዲየም ያስተናገደው አዳማ ከተማ ደግሞ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የአዳማ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ዳዋ ሆቴሳ እና ከነዓን ማርክነህ አስቆጥረዋል።

በትግራይ ስታዲየም ሀዋሳ ከተማን ያስተናገደው ስሁል ሽረ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ወደ ጂማ አቅንቶ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጅማ አባ ጅፋርን የገጠመው መቐለ 70 እንደርታ ደግሞ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

በተመሳሳይ ወልቂጤ ከተማ እና ባህር ዳር ከተማ በወልቂጤ ስታዲየም ባካሄዱት ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

በሶዶ ስታዲየም ድሬዳዋ ከተማን ያስተናገደው ወላይታ ዲቻ ደግሞ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ውጤቱን ተከትሎ ፕሪምየር ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ23 ነጥብ ሲመራ ፥መቐለ 70 እንደርታ ደግሞ በ22 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.