Fana: At a Speed of Life!

በ11 ወራት ከ3 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 11 ወራት ከ3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባድ እቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚንስቴር አስታወቀ፡፡
ባለፉት 11 ወራት በተሰራው ጠንካራ የኮንትሮባድን ቁጥጥር ሥራ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል ተብሏል፡፡
ከ2012 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወራት አፈጻፀም ጋር ሲነጻፀር በብር በ39 በመቶ ኮንትሮባንድን የመቆጣጠር አቅሜ ጨምሯል ነው ያለው ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ።
ከፍተኛ ውጤት እንዲመዘገብ ጥረት ላደረጉ አካላትም ምስጋና ማቅረቡን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
.
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.