Fana: At a Speed of Life!

በ200 ሚዜዎች ታጅቦ የተከናወነው የሰርግ ስነ ስርዓት

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በናይጀሪያ በ200 ሚዜዎች የታጀበ የሰርግ ስነ ስርአት ተከናውኗል።

ሳንድራ ኢኬጂ የተባለች ናይጀሪያዊ ስሟን በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ለማስፈር ሰርጓን በ200 ሚዜዎች በመታጀብ ማድመቋ ተሰምቷል።

በዚህም በብዙ ሚዜዎች ታጅቦ በተከናወነ የሰርግ ስነ ስርአት ከዚህ በፊት የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሽላለች።

በፈረንጆቹ 2012 ላይ ሰርጓን በ168 ሚዜዎች በማድመቅ ትዳር የመሰረተችው ቲና አክሌስ የተባለች አሜሪካዊት ስሟን በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ማስፈሯ ያታወሳል።

ሰሞኑን በናይጀሪያ ሌጎስ ከተማ በ200 ሚዜዎች በመታጀብ ትዳሯን የመሰረተችው ሳንድራ በአሜሪካዊቷ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን ማሻሻል መቻሏ ተነግሯል።

ሳንድራ በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ስሟን ለማስመዝገብም ለድርጅቱ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ማቅረቧ ነው የተገለጸው።

ይሁን እንጂ ድርጅቱ ሳንድራ ኢኬጂ በብዙ ሚዜዎች መታጀብ በሚለው ዘርፍ ክብረ ወሰን ማሻሻሏን እስካሁን ይፋ አላደረገም።

ምንጭ ፦ mywedding.co.ug”

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.