Fana: At a Speed of Life!

በ2012 ዓ.ም ተመራቂ ለነበሩ ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ ጥሪ ይደረጋል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተቋረጠዉን መደበኛ የገጽ-ለገጽ ትምህርትና ሥልጠናም ኮቪዲ-19ን በመከላከልን የሚከናወንበት ወቅት ላይ መደርሱንም የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ  ለፋና በላከው መግለጫ ÷ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተለይም ዩኒቨርሲቲዎችን በየጊዜዉ የዘርና የኃይማኖት ግጭት የሚቀሰቀስባቸዉ፣ የተማሪዎቻችን ነፍስ የሚጠፋባቸዉ፣ ልዩ ልዩ ማህበራዊ ጉዳቶች የሚከሰትባቸዉ እና ነጻና ገለልተኛ መሆን የሚገባቸዉ ተቋሞች የፖሊቲካዊ ይዘት ያላቸዉ ጣልቃ ገቢነት የበዛባቸዉ እንዲሆኑና የዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነታቸዉ ላይ ጫና የበዛባቸዉ እንዲሆኑ መደረጉን አስታውሷል፡፡

እንዲሁም ሕገ-ወጡ የጁንታ ቡድን ባለፉት ዓመታት ዩኒቨርሲቲዎችን በጎጥ ከፋፍሎ፤ ህብረ-ብሔራዊነትና ብዝሃነት እንዳይጎለብት፣ ተማሪዎች እና መምህራን በአከባቢ፤ በዘርና በኃይማኖት እንዲታጠሩ፤ ከህብረት ይልቅ መከፋፈሉ እንዲሰፋ በማድረግ ለሁከትና ለግጭት ብሎም የሰዉ ነፍስ እንዲጠፋ ሰፊ ሥራ ሰርቷል ብሏል፡፡

የተማሪ ወላጆችም ከራሱ አከባቢ ዉጪ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪ ምደባ ሲካሄድ ስጋታቸዉን በተለያዩ መንገድ ሲገልጹ ቆይተዋል  ብሏል ሚኒስቴሩ በመግለጫው፡፡

ይህ የሕገ-ወጡ ጁንታ ተልዕኮና ተግባራት ዳግም በዩኒቨርሲቲዎች ብሎም በአገራችን እንዳይከሰቱ ሕግ የማስከበር እርምጃ በጀግናዉ መከላከያ ሰራዊት እና በጸጥታ መዋቅሮች እንዲሁም በሕዝባችን ትብብር መወሰዱ ከልብ አስደስቶናል ያለው ሚኒስቴሩ ን ለዚህም እንኳን ደስ አላችሁ ብሏል፡፡

ይህን ተከትሎም  የተቋረጠዉን መደበኛ የገጽ-ለገጽ ትምህርትና ሥልጠና ኮቪዲ-19ን እየተከላከልን የምናከናወንበትና መንግሥት ለሚያቀርበዉ የሰብዓዊ ድጋፍ ጥሪ እንደጀመርነዉ ከልማት ሥራችን ጎን ለጎን አጠናክረን የምንቀጥልበት ወቅት ላይ ደርሰናል ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡

በዚህም ቅድሚያ ተማራቂ ተማሪዎችን በመቀበል የተማዎችን ጥሪ ከህዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚካሄድ እና  ከአንድ ሳምንት በኋላ ደግሞ ሌሎች ቀሪ ተማሪዎች እንዲገቡ እንደሚደረግ ገልጿል፡፡

 

በመሆኑም ሚኒስቴሩ የ2013 ትምህርትና ሥልጠና ዘመን የተሳካ እንዲሆን  የትምህርት መህበረሰቡ  የተለመደዉን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.