Fana: At a Speed of Life!

በ2013 አዲስ ዓመት ለህዝቦች የአደረጃጀት ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ መልስ ለመስጠት ይሰራል- አቶ ርስቱ ይርዳው

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ2013 አዲስ ዓመት ለህዝቦች የአደረጃጀት ጥያቄዎች ሰላማዊ መሆነ መንገድ መልስ ለመስጠት እንደሚሰራ የደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው ገለፁ።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው፥ የተጠናቀቀው በጀት ዓመት የክልሉን ሰላምና መረጋጋት በማስጠበቅ ህዝቡ ወደ ልማት ስራዎች ፊቱን እንዲያዞር ለማደረግ ተሰርቷል ብለዋል።

ከክልል ጀምሮ እስከ ቀበሌ መንግስታዊ መዋቅሩን በማጠናከር ሰላምና መረጋጋትን ማስፈን ላይ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውንም አስታውቅዋል።

በተጠናቀቀው አመት የአዲስ ክልል ምስረታንም በሰላማዊ መንገድ ማጠናቀቅ መቻሉን በማንሳት፤ ተቋማትን የማጠናከር ተግባራት እየተከናወነ እንደነበረም አስታውቅዋል።

ክልሉ በበጀት አመቱ ፊቱን ወደ ልማት እንዲመለስም ጥረቶች መደረጋቸውንም ነው ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ አቶ ርስቱ የተናገሩት።

እንዲሁም በጅምር የቀሩ ፕሮጀክቶች የፍጻሜ ሪቫን ቆረጣ ሁነት እንዲፈጸምላቸውም ተደርጓል ያሉት አቶ ርስቱ፥ 18 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ኢንቨስተሮች ወደ ተግባር መግባታቸውንም ተናግረዋል።

በ2013 ዓ.ም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ በአብሮነት የሚቆምበት እና የገበታ ለሀገር ሀገራዊ ፕሮጀክት ውጤትን የምናይበት ይሆናልም ነው ያሉት።

በዚህም በክልሉ የኮይሻ ፕሮጀክት ሂደት የሚጀመርበት እና በክልሉ የሚነሱ የህዝቦች የአደረጃጀት ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥበት ይሆናል ብለዋል።

የክልል አደረጃጀት ጥያቄዎች በሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ ብቻ ቀጣይ መፍትሄ ለማስቀመጥ እንደሚሰራም አንስተዋል።

የህዝቦችን አብሮነትን ያስቀደመ ወንድማማችነት እንዲጠናከር ያሳሰቡት ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ አቶ ርስቱ፥ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብም መልካም አዲስ አመትን ከወዲሁ ተመኝተዋል።

ሀይለየሱስ መኮንን

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.