Fana: At a Speed of Life!

በ2014 የኢትዮጵያ ውኃ ዋና ሻምፒዮን የአማራ ክልል አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 7፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በኢትዮጵያ ውኃ ዋና ሻምፒዮን አማራ ክልል በሁለቱም ፆታ አሸናፊ ሆኗል።
በቢሾፍቱ ከተማ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የነበረው የ2014 የኢትዮጵያ ውኃ ዋና ሻምፒዮን ዛሬ ተጠናቋል።
የአማራ ክልል በሁለቱም ፆታ አጠቃላይ አሸናፊ ሆኖ ሁለቱንም ዋንጫዎች ሲወስድ ክልሉ ለስፖርቱ ባበረከተው አስተዋፅኦ ልዩ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።
ኦሮሚያ ፖሊስ የውሃ ዋና ክለብ የፀባይ ዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን በወንዶች ጥላሁን አያል ከአማራ ክልል የሻምፒዮናው ኮኮብ ተጫዋች ተብሏል።
ብርሃን ደመቀ ደግሞ በሴቶች ከዳዊት እምሩ ኮንስትራክሽን ተቋራጭ ክለብ ኮኮብ ተብላለች።
ኮከብ አሰልጣኝ ማንደፍሮ ተገኝ ከአማራ ክልል ሆኖ ተመርጧል።
የኢትዮጵያ ውኃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን ውድድሩ ተተኪዎች የታዩበትና በቀጣይም በአፍሪካና ዓለም አቀፍ ውድድሮች አገሪቱን የሚወክሉ ስፖርተኞች አቅም የታየበት ነው ማለቱን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.