Fana: At a Speed of Life!

በ2019 በመረጃ መረብ ጥቃት 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ተመዝብሯል – ኤፍ ቢ አይ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ባሳለፍነው የፈረንጆቹ 2019 በዓለም ዙሪያ በመረጃ መረብ ጥቃት 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር መመዝበሩን የአሜሪካ የምርመራ ቢሮ (ኤፍ ቢ አይ) አስታውቋል።

የበይነ መረብ ወንጀል ቅሬታ ማዕከል (አይ ሲ 3) እንዳስታወቀው ወንጀሉ ተመሳሳይ ይሁን እንጅ ወንጀለኞች ድርጊቱን ለመፈጸም የሚጠቀሙበት ዘዴ የተለያየና ውስብስብ ነው።

ማዕከሉ በዓመቱ ውስጥ ከግለሰቦች እና ከንግድ ተቋማት 467 ሺህ 361 ቅሬታዎችን የተቀበለ ሲሆን፥ ከፈረንጆቹ 2000 ጀምሮ አምስት ሚሊየን ቅሬታወችን ማስተናገዱንም አስታውሷል።

በዚህም ወንጀለኞች በፈረንጆቹ 2019 ብቻ 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ከተለያዩ ተቋማት እና ግለሰቦች መመዝበራቸው ተመላክቷል።

ህጋዊ ኩባንያ መምሰል፣ ማጭበርበርና እና ዝርፊያ ድርጊቱን ለመፈጸም የሚጠቀሙባቸው መንገዶች መሆናቸውም ተገልጿል።

የጥቃት መንገዶች ይበልጥ የተራቀቁ እና ውስብስብ በመሆናቸው እውነተኛውን ከሀሰተኛው ለመለየት አስቸጋሪ እንዳደረገው ተጠቁሟል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.