Fana: At a Speed of Life!

በ2020 ወደ አየር የሚለቀቀው የበካይ ጋዝ መጠን መቀነሱ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኮቪድ ባሳደረው ተጸዕኖ አማካኝነት ወደ አየር የሚለቀቀው የበካይ ጋዝ መጠን መቀነሱን የአየር ንብረት ተመራማሪዎች አስታወቁ።

ይህም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ያልታየ መሆኑን ነው የተናገሩት።

በአውሮፓውያኑ 2020 የተመዘገበው ይህ ክብረወሰን የተባለለት ለውጥ በ7 በመቶ መውረዱ ነው የተገለጸው።

ፈረንሳይና እንግሊዝ ለሁለተኛ ዙር በወረርሽኙ መጠቃታቸውን ተከትሎ በአየር ንብረቱ ላይ ትልቅ ለውጥ እንደመጣ ተጠቅሷል።

በአንጻሩ በቻይና የአየር ንብረት ብክለቱ እየጨመረ መጥቷል ነው የተባለው።

ዓለም አቀፉ የካርበን ፕሮጀክት የተሰኘው ቡድን የካርበን ልቀቱ በዚህ ዓመት በ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ቶን መቀነሱ ነው የገለጸው።

ከዚህ ቀደም ካለው ጋር ሲነጻጸር የኢኮኖሚ መቀዛቀዙ ባየለበት በአውሮፓውያኑ 2009 ወደ ግማሽ ቢሊየን ሲቀንስ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ደግሞ አንድ ቢሊየን ቶን ወርዶ እንደነበረ ተመራማሪዎቹ ጠቅሰዋል።

እንዲሁም በየዓመቱ 39 ቢሊየን ቶን ካርበንዳይኦክሳይድ ወደ አየር እንደሚለቀቅ ነው ያነሱት።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.