Fana: At a Speed of Life!

በ24 ሰዓታት 943 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ23 ሰዎች ሕይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 14 ሺህ 540 የላብራቶሪ ምርመራ 943 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ይህን ተከትሎም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 25 ሺህ 118 መድረሱንም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ባወጡት መረጃ አመላክተዋል።

ከዚህ ባለፈ የ23 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 463 መድረሱንም አመላክተዋል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 338 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 11 ሺህ 34 መድረሱም ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.