Fana: At a Speed of Life!

በ3 ሚሊየን ዩሮ የተገነባው የብዝሃ ሳተላይት መረጃ መቀበያና መቆጣጠሪያ ጣቢያ ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የብዝሃ ሳተላይት መረጃ መቀበያና መቆጣጠሪያ ጣቢያ ተመረቀ፡፡

በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የተገነባው ማዕከል ምርቃት በእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪና ምርምር ማዕከል ነው የተከነዋነው፡፡

3 ሚሊየን ዩሮ ወጪ የተደረገበት ማዕከል ግንባታ በሶስት አመታት ውስጥ የተከናወነ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የሳተላይት መረጃ ፍላጎትን በዓይነት፣ በጥራትና በመጠን በማሟላት መረጃውን ለተለያዩ የልማት ተግባራት እንዲውል ያስችላል የተባለው ጣቢያ 7 ነጥብ 3 ሜትር ከፍታ አለው፡፡

የማዕከሉ ግንባታ በኢትዮጵያ በተበታተነ መልኩ የሚገኘውን የሳተላይት መረጃ በአንድ ማዕከል እንዲሆን ያስችላል ተብሏል።

ሳተላይት ካላቸው ሃገራት ጋር በነጻና በትብብር የውል ስምምነት በመፈጸም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የሳተላይት መረጃዎችን መጠቀም ያስችላል መባሉንም ኢዜአ ዘግቧል።

መረጃ መቀበያ ማዕከሉ ከአምስት የተለያዩ ዓለም አቀፍ የመሬት ምልከታ ሳተላይቶች እስከ 0 ነጥብ 5 ሜትር የምስል ጥራት ያለው የሳተላይት መረጃ መቀበል ያስችላል ተብሏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.