Fana: At a Speed of Life!

በ49 ሚሊየን ብር እድሳት የተደረገለት የአምባሳደር ፓርክ ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ49 ሚሊየን ብር እድሳት የተደረገለት የአምባሳደር ፓርክ በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡

በ1 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የአምባሳደር ፓርክ የእድሳት ስራ በ25 ወራት መጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ በ4 ሄክታር ቦታ ላይ በ101 ሚሊየን ብር የተገነባውና በመጀመሪያው የአዲስ አበባ ከንቲባ ስም የተሰየመው የቢትወደድ ወልደፃዲቅ ጎሹ መታሰቢያ ፓርክም በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡

በሁለቱም ፓርኮች ምርቃት ላይ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ፓርኮቹ አዲስ አበባን ውብና ፅዱ ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩ ከሚሰራቸው የአረንጓዴ ልማት ስራዎች መካከል ናቸው ተብሏል፡፡

በውስጣቸው ዘመናዊ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ የማንበቢያ ቦታዎችና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ተሟልተውላቸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.