Fana: At a Speed of Life!

በ6 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ የሚተገበር በሆርቲካልቸር ልማት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በ6 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ በሆርቲካልቸር ወይም በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ፕሮጀክት ይፋ ተደርጓል።

‘ወርልድ ቬጅቴብል’ ማዕከል ከኔዘርላንድስ የልማት ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው በአምስት አመት የአትክልት ልማት ስትራቴጂው ላይ የሚነጋገር አውደ ጥናት እያካሄደ ነው።

በመድረኩ በቀጣይ አምስት አመታት በኢትዮጵያና ኬንያ የሚተገበር “አትክልት ለሰዎችና ለአለማችን” የተሰኘ የሆርቲካልቸር ልማት ፕሮጀክት ይፋ ተደረጓል።

በአዲስ አበባና ናይሮቢ ከተማ ዙሪያ ባሉ የአትክልትና ፍራፍሪ ስራዎች ላይ የሚተገበረው ፕሮጀክቱ በከተሞቹ ዙሪያ ያሉትን ገበሬዎች፣ ወጣቶችና ሴቶች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የወርልድ ቬጅቴብል ማዕከል የኬንያና ኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር ራልፍ ሩትኸርት ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ በአነስተኛ ቦታ ትርፋማ የአትክልት ምርቶችን ማግኘት የሚያስችል የአመራረት ዘዴ፣ የዘር አይነቶችና የገበያ ትሰስር ለተጠቃሚዎች እንደሚፈጠር ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ በአምስት አመታት ውስጥ የሚተገበር መሆኑን ጠቁመው ÷ በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ያሉ 2ሺህ 400 አርሶ አደሮች የፕሮጀክቱ ቀጥታ ተሳታፊዎች እንደሚሆኑ እና ለ1 ሺህ 600 ወጣቶችና ሴቶች የስራ እድል እንደሚፈጠር ጠቁመዋል።

እነዚህ በፕሮጀክቱ ቀጥታ ተጠቃሚ የሚሆኑት እንጂ በሚፈጠረው ምርትና የገበያ ሂደት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህብረተሰብ ተጠቃሚ ይሆናል ብለዋል።

በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ ከሚያመጣው የገበያ ትስስር በየአመቱ እስከ 9 ሚሊየን ዩሮ ገቢ ሊገኝ ይችላል ሲሉም አክለዋል።

የሆርቲካልቸር ዘርፍ የሚያመጣውን ሰፊ የስራ እድልና ገቢ በማየት በግብርና ሚኒስቴር ራሱን የቻለ አደረጃጀት እንደተፈጠረለት የገለጹት  በሚኒስቴሩ የግብርና ግብአት ዘርፍ አማካሪ አቶ ደረጄ አሳምነው  መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የአትክልትና ፍራፍሬ ምርትን ለማስፋፋት የሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ የአመጋገብ ስርአትን ለማሻሻልና  የውጭ ምንዛሬ እጥረትን በመፍታት ረገድ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

በግብርና የ10 አመታት መሪ እቅድ ውስጥ በሆርቲካልቸር ዘርፍ ሰፊ ስራ ለመስራት መታቀዱን ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ ወርልድ ቬጅቴብል ማዕከል ከኔዘርላንድ የልማት ድርጅት ጋር ባደረጉት ድጋፍ የሚከናወን መሆኑ ታውቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.