Fana: At a Speed of Life!

በ60 ሀገራት የሚገኙ የአእምሮ ሕሙማን በቤታቸው ውስጥ ታስረው እንደሚውሉ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የአእምሮ ሕሙማን በቆሸሹ እና በተጣበቡ ቤቶች ውስጥ በገመድ ወይም በሰንሰለት ታስረው እንደሚውሉ ተገለጸ፡፡
ችግሩ ባስ ሲልም የአእምሮ ሕሙማኑን በእንስሳት ጉረኖ ውስጥ እስከማሰርና በዚያው እንዲመገቡና እንዲጸዳዱ እስከማስገደድም እንደሚደርስ ነው የተገለጸው፡፡
ሪፖርቱ የወጣው በትናንትናው ዕለት በተከበረውን የዓለም የአእምሮ ጤና ቀን ላይ ሲሆን÷ በሪፖርቱም በርካቶቹ የአእምሮ ሕሙማኑ የሚታሰሩት በቤተሰቦቻቸው፣ በአካባቢው ማኅበረሰብ ወይም በተቋማት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
እንደ ሪፖርቱ÷ የሚታሰሩት የአእምሮ ሕሙማን ምንም አይነት የሕክምና አገልግሎት በማያገኙበት ሁኔታ ሲሆን ÷ አብዛኛውን ጊዜ ሕሙማኑ ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት፣ ለነርቭ ጉዳት፣ ለጡንቻ መሸማቀቅ እና ከልብ ጋር ለተያያዙ ሕመሞች ይዳረጋሉ ብሏል፡፡
የአእምሮ ሕሙማንን በቤት ውስጥ በማሰር ከሚያውሉ 60 ሀገራት መካከል 24ቱ በአፍሪካ ውስጥ ያሉ ሀገራት እንደሆኑ መመላከቱን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.