Fana: At a Speed of Life!

በ80 ሚሊየን ብር የተገነባው የድሬዳዋ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጫና ዘመናዊ መናኸሪያ ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ80 ሚሊየን ብር የተገነባው የድሬዳዋ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጫና ዘመናዊ መናኸሪያ ተመርቋል፡፡

መናኸሪያውን መርቀው ስራ ያስጀመሩት በፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ያደታ፥ መናኸሪያው ሁለተኛው ዙር የህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት በተካሄደበት ማግስት መጠናቀቁ ለየት ያደርገዋል ብለዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋር በበኩላቸው፥ የመናኸሪያው መመረቅ ከዚህ በፊት በተጓዦች ይደርስ የነበረውን እንግልትና ዝርፊያ ያስቀራል ብለዋል።

የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬዳዋ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰአዳ አዋሌ በበኩላቸው፥ ቀደም ሲል የነበረው መናኸሪያ በክፍል ጥበትና በሚፈለገው መጠን ለተገልጋይ ተደራሽ የሆነ አገልግሎት ለመሰጠት ሲቸገር መቆየቱን ተናግረዋል።

በመሆኑም ተቋሙ አገልግሎት አሰጣጡን ወደ አዲሱ መናኸሪያ ማዘዋወሩ ብቃት ባላቸውና አዲስ አስተሳሰብ ባነገቡ ሰራተኞች የተሻለ የደንበኞች አገልግሎት ለማቅረብ እንደሚያስችለው ነው ያስታወቁት።

በ39 ሺህ ካሬ ሜትር ያረፈው የጎሮ መናኸሪያ በሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀ ሲሆን፥ ከ80 ሺህ በላይ ተገልጋዮችን የማስተናገድ አቅም እንዳለው በምረቃው ላይ ተገልጿል።

በእዮናዳብ አንዱዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.