Fana: At a Speed of Life!

ቡልቡላ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመንና ለማሳደግ ጉልህ ሚና ይጫወታል – አቶ መላኩ አለበል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡልቡላ የተቀናጀ የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ የግብርናውን ዘርፍ ለማያዘምንና ለማያሳደግ ጉልህ ድርሻ እንዳለው የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ተናገሩ፡፡

ባለሃብቶችና የግል አልሚዎችን በተሻለ ደረጃ ለመጥቀም ሙሉ ዝግጅቱን ያጠናቀቀው የቡልቡላ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክን የማስተዋወቅ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡

በመርሐ ግብሩ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል÷ የተቀናጁ የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ስራ መግባት በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ምርቶች ላይ እሴት በመጨመር የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አላቸው ብለዋል፡፡

በዘረፉ በተሰራ ሥራም ባለፋት ሁለት ዓመታት ውስጥ 17 ነጥብ 2 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ማግኘት መቻሉን ጠቁመዋል።

ወደ ቡልቡላ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ መግባት የጥሬ ዕቃዎች አቅርቦት እና የመሠረተ ልማት ችግር የሚያቃልል በመሆኑ የተፈጠረውን ምቹ አጋጣሚ ባለሀብቶችና የግል አልሚዎች እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል።

ፓርኩ መሰረተ ልማቶች በበቂ ሁኔታ አለመሟላት የተነሳ በታለመለት ጊዜ ስራውን ሳይጀምር መቆየቱ የተገለጸ ሲሆን ÷ አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ ስራውን ለመጀመር የሚችልበት አቋም ላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

ፓርኩ 135 ባለሀብቶችን የማስተናገድ አቅም እንዳለው መገለጹን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.