Fana: At a Speed of Life!

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ በ2012 በጀት አመት ከግብር በፊት 582 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ በ2012 በጀት አመት ከግብር በፊት 582 ሚሊዮን ብር ትርፍ አስመዘገቡን ገለጸ።

ባንኩ ባለፈው በጀት ዓመት በሃገር ደረጃ እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ ያጋጠሙትን ፈተናዎች በመቋቋም ከግብር በፊት 582 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን የባንኩ የዳይሬክቶሬት ቦርድ ሊቀመንበር ዶክተር ሰውአለ አባተ ገልጸዋል፡፡

ባንኩ በ2011 በጀት አመት ካተረፈው ትርፍ ጋር ሲነጻጸር የዘንድሮው 6ነጥብ 9 በመቶ ቅናሽ እንዳሳየ የተገለጸ ሲሆን፤ ለትርፉ መቀነስ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የውጭ ምንዛሬ ወደ ሃገር ውስጥ የሚልኩ ዜጎች መቀነስና መሰል የፋይናንሱ ዘርፍ መቀዛቀዝ እንደ ምክንያት ተጠቅሰዋል፡፡

ባንኩ በ2012 በተጠናቀቀው በጀት አመት የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑን በ3 ነጥብ 29 ቢሊዮን ብር ማሳደግ የቻለ ሲሆን ፤ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑም 13ነጥብ 88 ቢሊዮን ብር መድረሱን ዛሬ ባንኩ ባደረገው የባለ አክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ አስታውቋል፡፡

የባንኩን ካፒታል በተመለከተም የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት አንዳብራራው በበጀት አመቱ  503 ሚሊዮን ብር እድገት ያሳዬ ሲሆን፤  የባንኩን አጠቃላይ የካፒታል መጠን 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር አድርሶታል፡፡

እንደ ሪፖርቱ የባንኩ አጠቃላይ ሃብት በበጀት አመቱ የ4 ነጥብ 37 ቢሊዮን ብር እድገት ያሳየ ሲሆን ጠቅላላ ሃብቱም ወደ 18 ነጥብ 87 ቢሊዮን ብር መሆኑ ተገልጿል፡፡

በጸጋዬ ንጉስ

 

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.