Fana: At a Speed of Life!

ቡና ክብደትን ለመቀነስ እንደሚረዳ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ጥር 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቀን አራት ስኒ ቡና መጠጣት ክብደት ለመቀነስ እንደሚረዳ ተመራማሪዎች አስታወቁ፡፡

በቀን አራት ስኒ ቡና መጠጣት በሰውነት ውስጥ የሚገኝ ስብን ለማቃጠል እንደሚረዳ ጥናቱ አመልክቷል፡፡

ጥናቱ ከፍተኛ የሰውነት ክብደት ባላቸው በ126 ወንዶችና ሴቶች ላይ ለስድስት ወር በሲንጋፖር የተደረገ ነው፡፡

ከስድስት ወር በላይ በቀን አራት ስኒ ቡና የሚጠጡ ሰዎች በሰውነታቸው ከሚገኘው ስብ ውስጥ 4 በመቶ የሚጠጋ ቅናሽ ማሳየታቸው ጥናቱ አመልክቷል ፡፡

ቡና ውስጥ ያለው ካፌይን  የምግብ መፈጨት ስርዓት በማፍጠኑ ምክንያት በሰውነት ውስጥ የሚገኘው ስብ ሊቀንስ እንደቻለ ነው የተነገረው፡፡

በቀን አራት ስኒ ቡና መጠጣት የምግብ ፍላጎትን ለመቀነስ ሊረዳ ቢችልም ከፍተኛ የካፌይን ይዘት ስንወስድ  የራስ ምታትን ፣ መገጣጠሚያ  ችግር ፣ ፈጣን የልብ ምት እና የሆድ ህመምን ሊያስከትል ይችላልም ተብሏል፡፡

ቡና ጠጪ ያልሆኑ ሰዎች በዕለት ተዕለት በሚጠቀሙት ምግቦች፣መጠጦችና መድሀኒቶች ከ 4 ስኒ ቡና ጋር የሚስተካከል መጠን ያለው ካፌይን መጠቀም ይኖርባቸዋል ሲሉ በሃራቫርድ ቲ.ኤች ውስጥ የምግብ ጥናት ክፍል ባልደረባ የሆኑት ዶሪክ ጆንስተን አልፕሬ መክረዋል፡፡

ግኝቶቻችን ለማረጋገጥ ተጨማሪ ምርመራዎች እንደሚያስፈልጉ ተነግሯል፡፡

ዳላስ በሚገኘው የቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ጤና ትምህርት ቤት ዲፓርትመንት የፕሮግራም ዳይሬክተር እና ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ሳንሰን በበኩላቸው÷ ቡና በተለይ ካፌይን የምግብ ፍላጎትን ፣ የሰውነት ክብደትን እና የሰውነት ስብ መቀነስ ላይ ተፅዕኖ እንዳለው ይነገራሉ፡፡

ነገር ግን  በሰውነት ውስጥ የሚገኝን ስብ የሚቀይርበት አሰራር  አከራካሪ ነው ብለዋል፡፡

ምንጭ፡- ዬ ፒ አይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.