Fana: At a Speed of Life!

ቢሮው የሀረሪ ክልልን ሰላምና ፀጥታ አጠናክሮ ለማስቀጠል ከምስራቅ ዕዝና ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጋር እየሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በክልሉ ያለውን ሰላምና ፀጥታ አጠናክሮ ለማስቀጠል በደጀን ከሚገኘው የምስራቅ ዕዝ እና ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጋር የተቀናጀ ስራ እየተሰራ መሆኑን አስታወቀ።
የክልሉ ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ጥላሁን ዋደራ እንደገለጹት፥ የሸኔንና የህወሓት ተላላኪዎችንና ሰርጎ ገቦችን በመከታተል እንዲሁም ወደ ህግ በማቅረብ በኩል በደጀን ከሚገኘው የምስራቅ ዕዝ ፣ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከኦሮሚያ ፖሊስ እና ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት መስራት በመቻሉ በርካታ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡
በሐረሪ ክልል በተለያያ ጊዜ በተደረገ ፍተሻ የተለያዩ ወታደራዊ አልባሳት፣ የጦር ሜዳ መነፅሮች፣ የሳተላይት ስልኮች፣ መሳሪያና ጥይት በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፥ ምርመራው ተጠናክሮ ቀጥሏል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መነሻ በማድግ በክልሉ የተቋቋመውን ኮማንድ ፖስት የሚመሩት የምስራቅ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች፣ ሌሎች የፀጥታ ሃይሎችን በማስተባበር፣ በማሰማራት፣ መረጃ በመሰብሰብ እና በመተንተን አስፈላጊ በሆነባቸው አካባቢዎች ስምሪት በማድረግ የክልሉን ብቻ ሳይሆን የቀጣናውን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ሥራ እየተሠራ ነውም ብለዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.