Fana: At a Speed of Life!

ባህር አቋርጠው ሲጓዙ የነበሩ ከ700 በላይ የሚሆኑ ስደተኞች የህይወት አድን ሰራተኞች ታደጓቸው

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 26፣ 2013 ( ኤፍ ቢ ሲ) በሊቢያ እና ማልታ ዳርቻዎች ከ 700 በላይ የሚሆኑ ስደተኞች ባህር አቋርጠው ሲጓዙ የህይወት አድን ሰራተኞች ታድገዋቸዋል፡፡

በዚህ ሳምንት ከሊቢያና ማልታ ዳርቻዎች ስደተኞቹ የሜዲትራኒያን ባህርን አቋርጠው ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሲሞክሩ ነው በሕይወት አድን መርከበኞች የተደረሰባቸው ፡፡

ሕይወት አድን ሰራተኞቹ አራት መቶ የሚሆኑትን ስደተኞች ሕይወት ሊታደጉ የቻሉት በመካከለኛው የሜዲትራኒያን ባህር አካባቢ ሲሆን፥ የመቶዎቹ ሕይወት ሊተርፍ የቻለው ደግሞ ከማልታ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡

በሌሎች አራት ጀልባዎች የነበሩ ስደተኞችም በሕይወት አድን ሰራተኞች ሊተርፉ ችለዋል፡፡

አብዛኞቹ ስደተኞች ከሊቢያ ዳርቻዎች ተነስተው 300 ኪሎ ሜትሮች በማቋረጥ መዳረሻቸውን በአውሮፓ ከምትገኘው ጣሊያን ለማድረግ አስበው እንደነበርም ነው ለማወቅ የተቻለው፡፡

በዚህ ዓመት ብቻ ተመሳሳይ ሙከራዎችን በማድረግ የ900 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.