Fana: At a Speed of Life!

ባለሃብቶች ለተፈናቀሉ እና ዕርዳታ ለሚሹ ወገኖች የጀመሩትን ድጋፍ እንዲያጠናክሩ ተጠየቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለሃብቶች በሃገሪቷ የተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ እና ዕርዳታ ለሚሹ ወገኖች እያደረጉት ያለውን ድጋፍ እንዲያጠናክሩ የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ጠየቀ።

የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ባለሃብቶች ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎችን በማቅረብ ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

ባለሃብቶች አሁንም ለዜጎች ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ ድጋፉ በሚፈለገው ልክ ባለመሆኑ መጠናከር አለበት ብለዋል።

መተከል በተከሰተው መፈናቀል በመጠለያ ጣቢያ ለሚገኙት ተፈናቃዮች ድጋፍ በማድረግ አቶ በላይነህ ክንዴ፥ አቶ ወርቁ አይተነው እና ሌሎች ባለሃብቶች የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እያደረጉ መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

የእርዳታ ማዕቀፉ ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ አቅርቦቶችን በመያዙ ባለሃብቶች የሚያደርጉት ድጋፍ መንግሥት ሲያቀርብ የነበረውን መተካት እንደሚያስችል ገልጸዋል።

የባለሃብቶቹ ድጋፍ መንግሥት ተጨማሪ እርዳታ ለሚሹ ዜጎች እንዲደርስና ለድጋፍ የሚያውለውን ሃብት ለልማት ሥራ ለማዋል ያስችለዋል ነው ያሉት።

ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረግ ሕይወት ማቆያ ነው ያሉት ኮሚሽነር ምትኩ፤ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋምና ወደ መደበኛ ሕይወታቸው ለመመለስ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.