Fana: At a Speed of Life!

ባለስልጣኑ ለኢሳት ፃፈው ተብሎ የተሰራጨው ደብዳቤ ሀሰተኛ መሆኑን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን “በድል ዜና ዘገባዎች ላይ ጥንቃቄ እንዲደረግ ጥሪ ስለማቅረብ” የሚል ደብዳቤ ለኢትዮጵያ ሳትላይት ቴሌቭዥን(ኢሳት) አለመላኩን አስታውቋል፡፡

ህዳር 30 ቀን ጀምሮ በማህበራዊ ድረገፅ እየተሰራጨ የሚገኘው ይህ ሀሰተኛ መረጃ (ሀሰተኛ ደብዳቤ) ከባለሥልጣኑ ተልዕኮ ጋር ፍፁም የሚጣረስ መሆኑን ባለስልጣኑ አጥብቆ አስገንዝቧል፡፡

በመሆኑም ዜጎች ምንጩ ካልተረጋገጠና ሀሰተኛ መረጃ እራሳቸውን እንዲከላከሉ ፤ ለሌሎችም ባለማጋራት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንዲገቱ ባለስልጣኑ መክሯል፡፡

መረጃ አሰራጮችም ምንጩ ያልተረጋገጠ እና ሀሰተኛ መረጃን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አሳስበዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.