Fana: At a Speed of Life!

ባለስልጣኑ ሮም የገበታ ጨው እና ሴንሆን የማር ምርቶች የጤና ብቃት ማረጋገጫ የላቸውም አለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ሮም የገበታ ጨው እና ሴንሆን የማር ምርቶች የጤና ብቃት ማረጋገጫ ባለማግኘታቸው ከገበያ እየሰበሰቡ መሆናቸውን ገለጸ፡፡
በባለስልጣኑ ሮም የገበታ ጨው እና ሴንሆን ማር በሚል ስም የተገለፁት የምርት ውጤቶች ተገቢውን የጤና ብቃት ማረጋገጫ ሳያወጡ ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ በመስራታቸውና የምርቶቹ ናሙና ተወስዶ በላብራቶሪ ሲመረመር መስፈርቱን የማያሟላና ለጤና ጉዳት የሚያመጣ ሆኖ በመገኘቱ ከገበያ እንዲሰበሰቡ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ምርቱን የሚያመርቱት የድርጅቱ ባለቤቶችም በምርቶቹ ላይ የተሰጣቸው የእርምጃ ውሳኔ ተገቢ መሆኑን አምነው በቀጣይ ማሟላት የሚገባቸውን መስፈርት አሟልተው አዲስ ምርት አምርተው ወደ ገበያ እንደሚገቡ ከባለስልጣኑ ጋር መግባባት ላይ ደርሰዋል ተብሏል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.