Fana: At a Speed of Life!

ባለስልጣኑ አየር መንገዱን አስተማማኝ እና ተመራጭ የማድረግ ሚናውን ሊወጣ እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሰረተ- ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባለስልጣኑ አየር መንገዱን አስተማማኝ እና ተመራጭ የማድረግ ሚናውን ሊወጣ እንደሚገባ ጠቁሟል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስተማማኝ እና ተመራጭ እንዲሆን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ከፍተኛ ሚና እንዳለው ጠቁመው ፥ ተቋሙ ኢትዮጵያ ላቀደችው እድገት ቀልጣፋ እና ውጤታማ ለመሆን ጠንካራ ተቆጣጣሪ ተቋም ሆኖ መቀጠል ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

አያይዘውም የአየር ትራንስፖርት አደጋ ስጋትን መቀነስ ላይ የተሰራውን ስራ በጥንካሬ አንስተው ፥ በአንጻሩ ህብረተሰቡ አስተማማኝ የአየር ትራንስፖርት እንዲያገኝ ከማስቻል ረገድ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ማሟላት ጊዜ የሚሰጠው እንዳልሆነ አስገንዝበዋል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው መንግስቴ የተቋሙን የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ ፥ የሚገነቡ አውሮፕላን ማረፊያዎች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የሚጠብቁ መሆን ስላለባቸው የአውሮፕላን ማረፊያ ማስተር ፕላን ማዘጋጀት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውሮ በተመለከተበት ወቅት አገልግሎት በመስጠት ላይ ያለው ራዳር ረጅም ጊዜ ያገለገለ በመሆኑ እና የሚያስከትለውን አደጋ ከግንዛቤ በማስገባት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ችግሩ በአጭር ጊዜ ሊፈታ እንደሚገባ ማሳሰቡን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.