Fana: At a Speed of Life!

ባለስልጣኑ ከ800 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ የህክምና መድኃኒት ለሰራዊቱ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ለመከላከያ ሠራዊት የመድኃኒት አምራቾችን በማስተባበር ከ800 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ የህክምና መድኃኒቶችን ለመከላከያ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስረክቧል፡፡
 
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ ÷ ለሀገር ህልውና እየተፋለሙ ላሉና በጦርነቱ ለተጎዱ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የሚውል አይቪ ፍሉድ መድኃኒቶችን 9ሺህ ባግ የሚሆኑ ከ800 ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ መድኃኒቶችን በማሰባሰብ ድጋፍ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።
 
የባለስልጣኑ አመራሮችና ሰራተኞችም ለመከላከያ ሠራዊታችን ከወር ደመወዛቸው የተቻላቸውን አቅም ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሯ÷ በቀጣይም የተጀመረው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ድጋፉን የተረከቡት የሆስፒታሉ አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ተገኝ ለታ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ያደረገው ድጋፍ ለጀግናው ሀገር መከላከያ ሰራዊታችን የስነልቦናና ሞራልም ጭምር በመሆኑ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.