Fana: At a Speed of Life!

ባለፈው ዓመት የሚያበረታታ የወጪ ንግድ አፈጻጸም እና ቀጥተኛ የውጭ መዋዕለ ንዋይ ፍሰት ጭማሪ ታይቷል -ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፈው ዓመት የሚያበረታታ የወጪ ንግድ አፈጻጸም እና ቀጥተኛ የውጭ መዋዕለ ንዋይ ፍሰት ጭማሪ መታየቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄዱን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።
በዚህ ወቅትም ባለፈው ዓመት የሚያበረታታ የወጪ ንግድ አፈጻጸም እና ቀጥተኛ የውጭ መዋዕለ ንዋይ ፍሰት መጨመር መታየቱን ጠቅሰዋል።
ባለፉት ሁለት ወራት የዋጋ ግሽበት መቀነስ፣ ከፍተኛ የአረንጓዴ አሻራ ክንውን፣ የበጎ ፈቃደኝነት ተግባራት፣ ወደ ሀገር ውስጥ የሚላክ የውጭ ምንዛሬ ጭማሪ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥራ ክንውኖች የተመዘገቡበት እንደሆነም ነው ያስታወቁት።
በዚህ ዓመትም የተገኙ ስኬቶችን አጠናክሮ መቀጠል በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.