Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት ሦስት አመታት 2 ሺህ 50 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች መመሥረታቸውን ባለሥልጣኑ አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሦስት ዓመታት ብቻ 2 ሺህ 50 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች መመሥረታቸውን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን አስታወቀ።

ባለሥልጣኑ ዛሬ በሠጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፥ ከለውጡ በፊት እና በኋላ በአጠቃላይ 4 ሺህ ድርጅቶቾ ተመዝግበው በሥራ ላይ እንደሚገኙ ገልጿል።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጅማ ዲልቦ፥ ተቋሙ በአዲስ አዋጅ ሥራ ከጀመረ አንስቶ የዜጎችን የመደራጀት መብት እና የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሰፊ ሥራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

አሠራሮችን ማዘመን ፣ ተቋማዊ ግንባታ እና ተቋሙን በሰው ኃይል ማደራጀት እንዲሁም የበጎ አድራጎት ባሕልን ለማዳበር ሥርዓት መዘርጋት ላይ ሰፊ ሥራዎች መሰራታቸውንም አመላክተዋል።

በለይኩን ዓለም

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.