Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት ስምንት ወራት ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተይዘዋል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስምንት ወራት ከ 2 ቢሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮንትሮባንድ መቆጣጠርና ኦፕሬሽን ዳይሬክቶሬት አስታወቀ።
ኮሚሽነር አይንሻ ቶላ እንደገለፁት የፌዴራል ፖሊስ አባላት ህገ-ወጥ እንቅስቃሴውን ለመቆጣጠር ባደረጉት ጥረት የሚያዘው የእቃ ብዛትና መጠን ከአመት አመት እየጨመረ መጥቷል፡፡
ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀርም የ47 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ተናግረዋል።
የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ወደ ሀገር ቢገቡ በሀገርና በዜጎች ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራውን ህብረተሰቡ ሊያግዝና ህገ ወጥ እንቅስቃሴ ሲመለከት ጥቆማ ሊሰጥ እንደሚገባ ኮሚሽነሩ ማሳሰባቸውን ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.