Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት ስድስት ወራት ከ143 ቢሊየን ብር በላይ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ እና ወደ ፊት የሚገባ ብድርና እርዳታ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስድስት ወራት ከ143 ቢሊየን ብር በላይ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ እና ወደ ፊት የሚገባ ብድርና እርዳታ መገኘቱን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ኢትዮጵያ ከሁለት ዋና ዋና ምንጮች የውጭ ብድርና እርዳታ ለልማት ፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ እንደምታገኝ ገልጿል፡፡

አንደኛው ከበይነ-መንግሥታዊ ተቋማት እና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ሲሆን፤ ሁለተኛው ከመንግስታት ትብብር ምንጭ ነው፡፡

በዚህም በተፈፀሙ ስምምነት ቃል የተገባ እና የታቀዱ ስራዎችን ለማስፈፀም በቀጣዮቹ ከ3 እስከ 10 ዓመታት ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ 77 ነጥብ 33 ቢሊየን ብር ብድርና እርዳታ ተገኝቷል።

ከዚህ ውስጥ 17 ነጥብ 69 ቢሊየን ብሩ በብድር እንዲሁም 59 ነጥብ 64 ቢሊየን ብር በእርዳታ መገኘቱ ነው የተገለፀው።

በተመሳሳይ ቀደም ሲል እና ባለፉት ስድስት ወራት ከተገኘው ሀብት በግማሽ ዓመቱ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ የውጭ እርዳታ እና ብድር 66 ቢሊየን ብር መሆኑ ተጠቁሟል።

ከዚህ ውስጥ በብድር 29 ነጥብ 67 ቢሊየን ብር ሲሆን ቀሪው 36 ነጥብ 39 ደግሞ በእርዳታ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.