Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት ሶስት ሳምንታት ውስጥ ያለ ህጋዊ ሰነድ ወደ ሳኡዲ አረቢያ በመግባት በጂዳ እና በሪያድ በተለያዩ እስር ቤቶች የነበሩ 672 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት ሶስት ሳምንታት ውስጥ ያለ ህጋዊ ሰነድ ወደ ሳኡዲ አረቢያ በመግባት በጂዳ እና በሪያድ በተለያዩ እስር ቤቶች በከፍተኛ ችግር ውስጥ የነበሩ 672 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት እና የዲፕሎማሲ ስራዎች ጋር በተያያዘ መግለጫ ሰጥተዋል።
ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በቤይሩት ሊባኖስ በእስር ላይ የነበሩ 121 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች እና ከጎረቤት አገራት ጭምር ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን አምባሳደር ዲና አንስተዋል።
በመግለጫቸው ባለፉት ሳምንታት የተከናወኑ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴዎች በመግለጫቸው አንስተዋል።
በዚህም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በተመድ 75ኛ ዓመታዊ የሚኒስትሮች ስብሰባ እና በልማት ወደ ኋላ የቀሩ ሀገሮች በተካሄደው ዓመታዊ ስብሰባ ላይ በቪዲዬ ኮንፈረንስ መሳፋቸውን ገልጸዋል።
አቶ ገዱ በተገኙበት ከባለድርሻ አካለት ጋር በመተባበር መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ስለ ’’ገበታ ለሀገር’’ ፕሮጀክት እንቅስቃሴ ገለጻ መደረጉን ጠቁመዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.