Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት ቀናት በተደረጉ ፍተሻዎች የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ተይዘዋል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት ቀናት በተደረጉ ፍተሻዎች ከአንድ ሺህ በላይ ሽጉጥን ጨምሮ ቦምብ፣ ፈንጂ፣ የጦር ሜዳ መነጽር እና የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች መያዛቸው ተገለጸ።
 
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
 
ኮሚሽነሩ በመላ አገሪቱ በሚገኙ ከተሞች ጸጥታ የማደፍረስ ሙከራዎች ሊደረጉ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡
 
ችግሩን ለመከላከልም ጠበቅ ያለ የፍተሻ ስራ እንደሚሰራ መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
 
በሌላ በኩል በቅርቡ የታገዱ 14 የግል የጥበቃ ድርጅቶች ስር ተቀጥረው የሚሰሩ የጥበቃ ሰራተኞች ስራቸውን በጥንቃቄ እንዲያከናውኑ ኮሚሽኑ አሳስቧል።
 
በታገዱት ድርጅቶች ስር ተቀጥረው የሚሰሩ የጥበቃ ሰራተኞች ውስጥ ሰላማዊ የሆኑትን ሰላማዊ ካልሆኑት የመለየት ስራ እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመው፤ ውጤቱ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ አመልክተዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.