Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት አምስት ወራት ከማዕድን የወጪ ንግድ 241 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት አምስት ወራት ከማዕድን የወጪ ንግድ በተለይም ከወርቅ 241 ሚሊየን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ዑማ በማህበራ ትስስር ገፃቸው “አሁን ካለንበት ሀገራዊ ሁኔታ በተለይም በማዕድን አካባቢዎች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን ተቋቁመን የተመዘገው ገቢ አበረታች ነው” ብለዋል።

ያሉ ችግሮችን እየፈታን እና እየሄድንበት ያለውን መንገድ አጠንክረን ከቀጠልን የማእድን ምርታችን በተለይም የኢኮኖሚያችን ማገር መሆን እንደሚችል እየታየ ያለው ውጤት ማሳያ ነው ሲሉም በፅሁፋቸው አስፍረዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.