Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት አራት ወራት ከ107 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ2013 የበጀት ዓመት ከሀምሌ ወር እሰከ ጥቅምት 30 ባሉት አራት ወራት ውስጥ 107 ቢሊየን 627 ሚሊየን 206 ሺህ ብር ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው አስታወቁ።

በአራት ወራቱ 104 ቢሊየን 574 ሚሊየን 996 ሺህ ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ107 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የገለፁት ሚኒስትሩ አፈፃፀሙም 103 በመቶ አንደሆነ ገልፀዋል።

ይህ አፈጻፀም ከ2012 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር ሲታይ 17 ቢሊየን 319 ሚሊየን 722 ሺህ ብር ብልጫ እንዳለው ተጠቁሟል።

በዚህም  75 ቢሊየን 78 ሚሊየን 276 ሺህ ብሩ ከሀገር ውስጥ ታክስ ፣ ከወጭ ንግድና ቀረጥ 36 ቢሊየን 465 ሚሊየን 161 ሺህ ብር እና ከሎተሪ ሽያጭ 83 ሚሊየን 768 ሺህ ብር የተጣራ ገቢ መገኘቱን አቶ ላቀ አስታውቀዋል።

ይህ መልካም ውጤት የተመዘገበው በሁሉም ባድርሻ አካላት ተሳትፎ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሩ ዓለም አቀፉ ወረርሽንና የወቅቱ የሀገሪቱን ሁኔታ ተፅዕኖ ሳያሳርፍባቸው ፣ ግብርን ለመሰወር በምክንያት የሚያገለግሉ ክስተቶችን ሰበብ ሳያደርጉ ኃላፊነታቸውን ግብር ከፋዮች ምስጋና አቅርበዋል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.