Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት አስር ወራት ውስጥ ከ198 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2012 በጀት ዓመት አስር ወራት ውስጥ 198 ቢሊየን ብር 477 ሚሊየን 959 ሺህ ብር ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው አስታወቁ።

በ2012 የበጀት አመት ከ270 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።
በዚህም ባለፉት አስር ወራት ሲሆን በ10 ወር ውስጥ 198 ቢሊየን ብር 477 ሚሊየን 959 ሺህ ብር ገቢ በመስብሰብ የአመቱን ዕቅድ 73 ነጥብ 5 በመቶ ማሳካት መቻሉን ነው የተነገረው።

ይህም ከ2011 በጀት አመት ተመሳሳይ 10 ወራት ጋር ሲነፃፀር በ2 ቢሊየን 941 ሚሊየን 613 ሺህ ብር ብልጫ አለው ተቧል።

ሚኒስትሩም ለዚህ ስራ ስኬት አስተዋፅኦ ላበረከቱ አመራሮችና ባለሞያዎች እንዲሁም በወቅቱ ግብራችውን ለከበሉ ዜጎች ምስጋና አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.