Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ571 ሚሊየን በላይ ኪሎ ዋት ሰዓት የሃይል ብክነት መቀነስ ተቻለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ571 ሚሊየን በላይ ኪሎ ዋት ሰዓት የሃይል ብክነት መቀነስ መቻሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2013 በጀት አመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ቴክኒካልና ቴክኒካል ያልሆነ የሃይል ብክነትን ለመከላከል ባደረገው የክትትልና ቁጥጥር ስራ 571 ሚሊየን 714 ሺህ 689 ኪሎ ዋት ሰዓት የኢነርጂ ሃይል ከብክነት ማዳን የቻለ ሲሆን ይህም 135 ሚሊየን 856 ሺህ 871 ብር ዋጋ ያለው ነው፡፡

ተቋሙ የሃይል ብክነቱን መቀነስ የቻለው የኤሌክትሪክ ስርቆትን በመከላከል፣ በትክክል የማይሰሩ፣ የተቃጠሉ፣ የቆሙ ቆጣሪዎች በወቅቱ እንዲቀየሩ በማድረግ፣ የታሪፍ ለውጥ የሚያስፈልጋቸውን ደንበኞች የታሪፍ ለውጥ በማድረግ፣ ቢል የማይወጣላቸው ደንበኞችን ወደ ሲስተም እንዲገቡ በማድረግ፣ ያልተፈቀደ የኃይል ጭነትን በመቆጣጠር፣ ከቆጣሪው ልኬት ውጪ የተገጠመ አውቶማቲክ ፊዩዝን በመቀየር፣ የዝቅተኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪ ደንበኞች የተገኘ የማባዣ ስህተት በማስተካከል፣ የገቢ ደረሰኝ የሌላቸው እንዲኖራቸው በማድረግ እና የመሳሰሉ ቴክኒካል ያልሆነ የሃይል ብክነትን ለመቀነስ የሚያስችሉ ስራዎችን በመስራት መሆኑን ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ተቋሙ ቴክኒካል የሆኑ የሃይል ብክነቶችን ለመቀነስ 2 ሺህ የሚሆኑ የ ሲ ኤም አር አይ የቆጣሪ ማንበቢያ መሳሪያዎችን በተስተካከለው የሶፍትዌር ዲዛይን በመጫን ወደ ስራ ያስገባ ሲሆን ከ50 ሺህ ያላነሱ ዘመናዊ ቆጣሪዎችን ለመግጠም ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

ተቋሙ ሊከሰት የሚችለውን የሃይል ብክነት ለመቀነስ የደንበኞች ቆጣሪ ቅያሪ ስራ ማከናወን፣ የደንበኞችን መረጃ ወደ አዱሱ ሲሰተም ማዛወር እና ሌሎች ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱ ተጠቁሟል።

በበጀት አመቱ ቀጣይ ሶስት ወራት ሊከሰቱ የሚችሉ ቴክኒካልና ቴክኒካል ያልሆኑ የሃይል ብክነቶችን ለመቀነስ ሰፊ እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝም ነው የተነገረው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.