Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 1 ሺህ 186 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው የ20 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 21 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ለ18 ሺህ 060 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1 ሺህ 186 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።
 
ከዚህ ባለፈም ባለፉት 24 ሰአታት የ 20 ሰዎች ህይወት ማለፉን የገለፁት ሚኒስትሯ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 745 ደርሷል።
 
በተጨማሪም ባለፉት 24 ሰአታት 518 ሰዎች ሲያገግሙ ይህን ተከትሎም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 16 ሺህ 819 ደርሷል።
 
አሁን ላይ 330 ሰዎች ደግሞ በፅኑ ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛሉም ነው ያሉት።
 
በኢትዮጵያ እስካሁን ለ831 ሺህ 470 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 46 ሺህ 407 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።
 
ከዚህ ውስጥ 16 ሺህ 819ኙ ሲያገግሙ 28 ሺህ 831 ሰዎች ደግሞ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
 
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.