Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 294 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተካሄደ የ5 ሺህ 186 የኮሮና ቫይረስ ምርመራ 294 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።

የጤና ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ዶክተር ተገኔ ረጋሳ ለፋ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቁት በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 8 ሺኅ 475 ደርሷል።

ዶክተር ተገኔ በአሁን ወቅት 36 ፅኑ ህሙማን እንደሚገኙ በመግለፅ ባለፉት 24 ሰዓታት 51 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል።

እንዲሁም የ2 ሰዎች ህይወት ማለፉ ነው የተነገረው።

ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ የተገኘባቸው 209 ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፣ 31 ከትግራይ ፣ 20 ከጋምቤላ ፣13 ከአማራ ፣6 ከአፋር ፣ 2 ከሶማሊ ክልሎች እና 4 ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር መሆናቸውን ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ እስከአሁን ድረስ 302 ሺህ 728 የኮሮና ቫይረስ ምርመራ የተደረገላቸው ይገኛል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል  4 ሺህ 768 ያገገሙ ሲሆን 3 ሺህ 557 ሰዎች የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ነው ዶክተር ተገኔ ያስታወቁት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.