Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 950 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 24 ሺህ 544 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 950 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ በእለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርቱ በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 57 ሺህ 466 መድረሱን አመልክቷል።

በሌላ በኩል በ24 ሰዓታት ውስጥ 164 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 20 ሺህ 776 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

17 ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎም አጠቃላይ በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 897 ደርሷል።
በአሁኑ ወቅት 326 ሰዎች በበሽታው በፅኑ ታመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.