Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 1ሺህ303 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ24 ሰዎች ሕይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 23 ሺህ 712 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 303 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 56 ሺህ 516 መድረሱንም የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ያወጡት መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ ባለፈም በ24 ሰዓታት ውስጥ የ24 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 880 መድረሱንም አመላክተዋል።

በትናንትናው እለት 329 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፤በአጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 20 ሺህ 612 መድረሱን ሚኒስትሯ ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል 315 ሰዎች ፅኑ ህሙማን የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

እስካሁን ለ994 ሺህ 303 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን አሁን ለ 23 ሺህ 22 ሰዎች ህክምና እየተደረገ ይገኛል፡፡

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.