Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 1 ሺህ 9 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ16 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 19 ሺህ 364 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 1 ሺህ 9 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ ።
 
ሚኒስቴሩ በዕለታዊ መግለጫው በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 52 ሺህ 131 ደርሷል።
 
በሌላ በኩል 612 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 18 ሺህ 994 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
 
በ24 ሰዓታት ውስጥም የ16 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ያንንም ተከትሎ በሀገሪቱ በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 809 ደርሷል።
 
እንደ ሚኒስቴሩ መግለጫ በአሁኑ ወቅት 344 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት በፅኑ የታመሙ ሲሆን እስከ አሁን በአጠቃላይ ለ910 ሺህ 293 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጓል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.