Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 281 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 553 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 4 ሺህ 171 የላቦራቶሪ ምርመራ 281 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ዶክተር ሊያ በፌስቡክ ገጻቸው እንደገለጹት 553 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

እንዲሁም ባለፉት 24 ሰዓታት በቫይረሱ ምክንያት 3 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

እስካን ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች 109 ሺህ 846 ሲደርስ 1 ሺህ 912 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ቫይረሱ ያለባቸው 11 ሺህ 385 ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 231 ሰዎች ደግሞ በጽኑ የታመሙ መሆናቸውን ነው የገለጹት፡፡

ወረርሽኙ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ ለ1 ሚሊየን 785 ሺህ 132 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል፡፡

ከእነዚህም መካከልም 123 ሺህ 145 በወረርሽኙ የተያዙ ሲሆን አሁን ላይ 11 ሺህ 385 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.