Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 400 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 981 ከቫይረሱ አገግመዋል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 2፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ባለፉት 24 ሰዓታትም ውስጥ በተደረገው 5 ሺህ 181 የላብራቶሪ ምርመራ 400 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 100 ሺህ 727 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ያወጣው እለታዊ መረጃ ያመለክታል።
ከዚህ ባለፈ የ8 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 545መድረሱንም አመላክተዋል።
በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 981 ሰዎች ከኮሮና ቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 62 ሺህ 497 መድረሱም ተገልጿል።
ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ1 ሚሊየን 539 ሺህ 653 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 100 ሺህ 727 ደርሷል።
አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 36 ሺህ 683 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 292 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.