Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 433 የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ11 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 647 ደርሷል።

ተጨማሪ 433 ሰዎች ኮሮና ቫይረሱ ሲገኝባቸው፣ 157 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 4 ሺህ 495 የላቦራቶሪ ምርመራ 433 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 105 ሺህ 785 ደርሷል።

በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 65 ሺህ 691 ሆኗል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 38 ሺህ 445 ሰዎች መካከል 333 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በአገሪቱ እስካ ዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 595 ሺህ 643 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.