Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 477 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 838 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 5 ሺህ 605 የላቦራቶሪ ምርመራ 477 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ዶክተር ሊያ በፌስቡክ ገጻቸው እንደገለጹት 838 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

እንዲሁም ባለፉት 24 ሰዓታት በቫይረሱ ምክንያት 13 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

እስካሁን በወረርሽኙ ምክንያት 2 ሺህ 116 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ቫይረሱ ያለባቸው 12 ሺህ 937 ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 228 ሰዎች ደግሞ በጽኑ የታመሙ መሆናቸውን ነው የገለጹት፡፡

ወረርሽኙ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ ለ1 ሚሊየን 974 ሺህ 373 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል፡፡

ከእነዚህም መካከልም 138 ሺህ 861 በወረርሽኙ የተያዙ ሲሆን አሁን ላይ 12 ሺህ 937 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.