Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 486 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ 7 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 7ሺህ 227 የላብራቶሪ ምርመራ 486 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 72 ሺህ 173 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ያወጣው ዕለታዊ መረጃ ያመለክታል።
ከዚህ ባለፈ ባለፉት 24 ሰዓታት የ 7ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 155 ደርሷል።
አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 41 ሺህ 153 ሲሆኑ፥ ከእነዚህም ውስጥ 273 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
በዛሬው እለትም 402 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን ÷በአጠቃላይ በኢትዮጵያ 29 ሺህ 863ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል።
እስካሁን ድረስ 1 ሚሊየን 241 ሺህ 872 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጓል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.