Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 767 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 7 ሺህ 394 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 767 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
 
በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 83 ሺህ 429 ደርሷል።
 
በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት በቫይረሱ አማካኝነት የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
በዚህም በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎቸ ቁጥር 1 ሺህ 277 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በትዊተር ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት መረጃ ያመለክታል።
በ24 ሰዓታት ውስጥ 581 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 37 ሺህ 683 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
እንዲሁም 239 ሰዎች ፅኑ ህሙማን ማዕከል ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል ተብሏል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.